የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያቀላጠፈ ነው 

Apr 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በሆሳዕና ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያቀላጠፈ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ።

በከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ምቹ ከተሞችን ለመፍጠር የላቀ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል።

በተለይም ቀደም ሲል በከተሞች ይስተዋል የነበረውን የመሠረተ ልማት ቅንጅት ማነስ በማስቀረት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና የተቀናጀ ከተማ ለመገንባት መሠረት እየጣለ ነው።

በሆሳዕና ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ የከተማዋ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እንዲቀላጠፍ ማስቻሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

አስተያየታቸውን ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል የቦቢቾ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ደስታ ኤርቻዮ፤ ልማቱ የነዋሪውን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።


የኮሪደር ልማቱ ለነዋሪው ምቹ የመኖሪያና የመዝናኛ ስፍራዎችን ማስገኘቱን ጠቅሰው፣ ልማቱ ከተማዋን ከመቀየር ባለፈ ቀደም ሲል በምሽት ለመንቀሳቀስ ሥጋት የነበሩ አካባቢዎችን ችግር መቅረፉንና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያግዙ ማዘውተሪያዎችን በማካተቱ ዜጎች ጤናቸውን እንዲጠብቁ ማገዙን ገልጸዋል።

የአራዳ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ጌታሁን አበራ በበኩላቸው፣ ልማቱ ከተማዋ ውበት እንድትላበስ ከማድረጉም ባለፈ የመንገድና የመብራት ችግሮች እንዲቀረፉ አድርጓል ብለዋል።


ልማቱ በእግር ለመጓዝ በሚያመች መልኩ በመቀየሩና የከተማዋን የጽዳት ሥርዓት በማሻሻሉ መንግሥት ለሕዝቡ የገባውን ቃል በተግባር ያረጋገጠበት ሥራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሌላኛዋ ነዋሪ ወይዘሮ ታገሰች ጋርከቦ ፤ ልማቱ በእግር ተንቀሳቅሰው ማኅበራዊ ጉዳዮቻቸውን እንዲያስፈጽሙ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።


ወጣት ስንዳው ጀንበሩ ደግሞ የብስክሌት መንገድ መገንባቱ የትራፊክ መጨናነቅን ከመቀነሱም በላይ ብስክሌት አሽከርካሪዎች ያለምንም ሥጋት እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል ብሏል።


የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እንደገለጹት፤ የከተማውን የውስጥ አቅምና የማኅበረሰቡን ተሳትፎ በማቀናጀት የ35 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለመሥራት ታቅዶ ወደ ትግበራ ተገብቷል።


በመጀመሪያው ምዕራፍ ከታቀደው 24.5 ኪሎ ሜትር ውስጥ 12 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትሩ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃ ሲሆን፣ ሥራው ምቹ የእግረኛ መንገዶችን፣ የአካል ጉዳተኞች መሄጃን፣ የብስክሌት መንገድንና የመብራት መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው ብለዋል።

ልማቱ የአካባቢን ጽዳት ባህል ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ከንቲባው አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026