የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የመዲናዋ ትንሣኤ የአፍሪካ ከተሞችን ሥልጣኔና ዕድገት ለማፋጠን አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ ነው

Apr 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ ትንሣኤ የአፍሪካ ከተሞችን ሥልጣኔና ዕድገት ለማፋጠን አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ መሆኑን የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አባል ሀገራት ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ።

የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አባል ሀገራት ጉባዔ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን የልማት ሥራዎች በጎበኙበት ወቅት የጅቡቲ፣ የሱዳን እና የዛምቢያ ልዑክ አባላት ሀሳባቸውን ለኢዜአ አጋርተዋል።

ከአሥር ዓመታት በፊት መዲናዋን የጎበኙትና ከጅቡቲ የመጡት ኢሳም አብዱልሃኪም፤ ያኔ በአዕምሯቸው የተቀረጸው የአዲስ አበባ ደብዛዛና ጎስቋላ ገፅታ ዛሬ ላይ ተቀይሮ ማየታቸውን በአግራሞት አስታውሰዋል።


በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ በበአጭር ጊዜ የተከናወኑት አስደናቂ የልማት ሥራዎች አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጎብኝዎቿ ደግሞ ማራኪ እንድትሆን አድርጓል ብለዋል።

በተለይም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የልማቱ የመዲናዋን የኢኮኖሚ አቅም ከማሳደጋቸውም ባሻገር ዓለም አቀፍ የከተሜነት የውድድር መስፈርቶችን እንድታሟላ እንዳስቻላት ገልጸዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራትና በፈጣን ልማት የተመዘገቡ ውጤቶች አዲስ አበባን በጽዳታቸውና ውበታቸው ከሚጠቀሱ የዓለም ታላላቅ ከተሞች ተርታ እንድትሰለፍ እንዳደረጋት ተናግረዋል።

በቆይታቸው ወቅት ከነዋሪዎች የተቸራቸው የከበረ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስም የኢትዮጵያውያንን ጥልቅ ትብብርና በጎነት በሚገባ የተመለከቱበት አጋጣሚ መሆኑን አንስተዋል።

ከሱዳን የመጡት እስማዔል አሊ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ አስደናቂ የለውጥ ጉዞ የአፍሪካ ከተሞችን ወደላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ ትምህርትና ተሞክሮ እንደሚሆን ገልጸዋል።


በአሁኑ ወቅትም አዲስ አበባ በአፍሪካ ስሉጥ ከሆኑ ዘመናዊ የከተማ ፈርጦች መካከል መሰለፏን በጉብኝታቸው እንደታዘቡ ተናግረዋል።

በመዲናዋ ቆይታቸውም በኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተመዘገበው እመርታ ከተማዋ በዕድገት ጎዳና እየገሰገሰች መሆኗን እንዳረጋገጡ አንስተዋል።

ከዛምቢያ የመጡት መሲ ችሉ፤ የአዲስ አበባ አስደናቂ የልማት ስኬት በራስ አቅምና ቀለም መገንባቱ ዘርፈ ብዙ ትርጉም የሚሰጠው የመቻል ውጤት ነው ብለዋል።


ይህም ለአፍሪካዊያን ያለአንዳች እርዳታና ጥገኝነት የላቁና የሰለጠኑ ከተሞችን መገንባት እንደሚቻል ትምህርት እንደሚሰጥ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026