የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለአፍሪካ አገራት ትልቅ አርአያ ናቸው - የላይቤሪያ ልዑካን ቡድን

Apr 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አርአያ ናቸው ሲሉ የላይቤሪያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት ገለፁ።

ልዑኩ ዛሬ፣ የግብርና እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ ዘመናዊ መስኖን መሰረት ያደረገ የከተማ ግብርና እንዲሁም የእንስሳትና የዶሮ እርባታ ልማት ሥራዎችን በቢሾፍቱ የመስክ ምልከታ አድርጓል።


የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሳሙኤል ኮፊ ዉድስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተከተለች ያለው መንገድ እጅግ ተራማጅ ነው።

ላይቤሪያም የኢትዮጵያን ተሞክሮ በመቅሰም ዩኒቨርሲቲዎቿን፣ ወጣቶችን እና ማህበረሰቡን በስፋት በማሳተፍ ለምግብ ምርትና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ውጤቶችን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።

በተለይም በግብርናው ዘርፍ የታየው የወጣቶች ተሳትፎ በአፍሪካ ለሚታየው የስራ አጥነት ችግር ትልቅ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቶች ትኩረታቸውን ከቢሮ ስራ ወደ ግብርና በማዞር የወደፊት ህይወታቸው ለመዘጋጀት የሚያደርጉት ጥረት ለጠቅላላው አፍሪካ ወሳኝ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት ከተመለከቷቸው የኢትዮጵያ እርሻ ውጤቶችና ከታየው ተነሳሽነት ትልቅ ልምድ መቅሰማቸውንም አረጋግጠዋል።


የላይቤሪያ የኢንፎርሜሽን ምክትል ሚኒስትር ዳንኤል ኦ. ሳንዶ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር ለመላው አፍሪካ አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በተካሄደው ውይይት፤ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምግብ ዋስትናን የቀዳሚነት አጀንዳዋ አድርጋ መነሳቷን መረዳታቸውን ጠቁመዋል።

ራሷን መመገብ የማትችል ሀገር መሰረቷ ደካማ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የጀመረችው ተራማጅ የዕድገት ጎዳና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በኢትዮጵያ በመስኖ ቴክኖሎጂ የታገዘ የግብርና ሥራ መከናወኑና በዚህም በርካታ ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የውጭ ምርትን በመቀነስና የግብርና ምርቶቿን ወደ አውሮፓ ገበያ በመላክ የንግድ ሚዛኗን ለማስተካከል የምታደርገውን ጥረትም አድንቀዋል።

ሀገራቸው በምግብ ራሷን እንድትችል ለማድረግ የኢትዮጵያን ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉም አክለዋል።


የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሌይሊ ፊሊፕስ ማፓርየን (ዶ/ር) ፣ እዚህ ያየሁት የግብርና ኢንዱስትሪ የዳበረና የአገሪቱን ልማት በብቃት እየደገፈ መሆኑን ተረድቻለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቆይታዬ ወደ ላይቤሪያ ይዤው የምመለሰው ብዙ ትምህርት ሰጥቶኛል ያሉት የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፤ ጉብኝቱ በላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የግብርና ፕሮግራም እንዴት ማዘመን እነደሚቻል እንዳስብ አድርጎኛል ብለዋል።

የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በሰጡት ማጠቃለያ፤ ኢትዮጵያ ጸጋዎቿን በመጠቀምና በማቀናጀት ያከናወናቸው የልማት ተግባራት ለአፍሪካውያን ምሳሌ እንደሚሆኑ የልዑካን ቡድኑ እንዳነሱላቸው ገልጸዋል።


በቀጣይ የላቤሪያ የግብርና ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026