🔇Unmute
ሚዛን አማን፣ ሚያዝያ 8/2018 (ኢዜአ)- የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ እንዲሳካ ዜጎች ዓለም አቀፍ ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ሊያጠናክሩ ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ።
የቀጣናው ሀገራትም ከሌሎች ጫና በመላቀቅ የመተባበር እና በሰጥቶ መቀበል መርህ አብሮ የመልማት አማራጭን ሊተገበሩ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከግብ እንዲደርስ ዜጎች በያሉበት ዓለም አቀፍ ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ማጠናከር አለባቸው፡፡
በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ቢመርቅ በሪሁን እንዳሉት ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ሁሉም በሚገባ ሊያውቀው ይገባል።
የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ብሔራዊ ጉዳይ በመሆኑ ከግብ እንዲደርስ የዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ በያሉበት ዓለም አቀፍ ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ አስተዋጿቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።
"እንደሀገር ባጋጠመ የፖለቲካ ስብራት ከባህር በር ተነጥለን ቆይተናል፤ ይህ ስህተት ነው" ያሉት መምህሩ፣ ስህተቱን ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ለማረም የተጀመረውን እንቅስቃሴ ሁሉም በቁርጠኝነት መደገፍ አለበት ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ሕጎችና ሥርአቶች በሚፈቅዱት የድርድርና የሰጥቶ መቀበል መርህ መሰረት የወደብ ባለቤትነት ታሪክን ዳግም ለማደስ የሚያስችል የትውልድ እንቅስቃሴ ላይ መድረሱ ትልቅ ሀገራዊ ለውጥ መሆኑንም አንስተዋል።
እንደ መምህር ቢመርቅ ገለጻ የሀገራት ሉዓላዊነት በተጠበቀ መልኩ ሌሎች ሀገራትም የባሕር በር የማግኘት መብት ስላላቸው የቀጣናው ሀገራት ትብብርን ከጋራ ተጠቃሚነት ጋር በማስተሳሳር ሊያዩት ይገባል።
ለዚህም ፖለቲከኞች፣ ዳያስፖራው፣ ምሁራን እና ሌሎችም ዜጎች በያሉበት የሚያደርጉትን ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አጠናክረው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል።
"ማንም ዜጋ ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥቶ የመሥራትና የመታገል ኃላፊነት አለበት" ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህር ሙሉቀን አየለ ናቸው።
ሀገር በዜጎች ድምር ጥረት ጥቅሟን ማስጠበቅና ከፍ ማለት እንደምትችል ገልጸው፣ የዛሬው ትውልድ አጀንዳ ለሆነው የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ገለልተኛ ሊሆን እንደማይችል አንስተዋል።
በመሆኑም የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄው ከግብ እንዲደርስ ሁሉም ያለቅድመ ሁኔታ አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ አለበት ብለዋል።
እንደ ዩኒቨርሲቲ መምህርነታቸው ለጉዳዩ ይጠቅማሉ የሚሏቸውን ሀሳቦች በማቅረብና አስቻይ መንገዶችን በማመላከት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026