🔇Unmute
ጂንካ፤ ሚያዚያ 10/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት ማሳደጉን የጂንካ ከተማ ሰልጣኞች ተናገሩ።
መንግስት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክህሎት አቅምን በማሳደግ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለመ ስልጠና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እየሰጠ ይገኛል።
በጂንካ ከተማ ስልጠናውን የተከታተሉ ሰልጣኞችም የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከቴክኖሎጂ ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ እንዳገዛቸው ለኢዜአ ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪ ወጣት በረከት አባይነህ በኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና ከተካተቱ አራት ኮርሶች ሙሉውን በማጠናቀቅ ሰርተፊኬት መውሰዱን ገልጿል።
በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ፣ በፕሮግራሚንግ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የስልጠና መስኮች በቂ ዕውቀት ማግኘቱን ተናግሯል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከቴክኖሎጂ ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ እንዳገዛቸው የገለፀችው ደግሞ ወጣት ምህረት ፍሬው ናት።
ከፕሮግራሚንግ በቀር ሦስት ኮርሶችን በማጠናቀቅ ሰርተፊኬት መውሰዷን ገልፃ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት በእጅጉ የሚያሳድግ ጠቃሚ ስልጠና መሆኑን ተናግራለች።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ከፍታ ለመረዳት ያስችላል ያለው ደግሞ ወጣት በቃሀኝ ጥላሁን ነው።
በወሰዳቸው የፕሮግራሚንግ እና የዳታ አናሊስስ ስልጠናዎች ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚያስችለውን የዲጂታል ዕውቀት ማሳደግ መቻሉን ገልጿል።
መንግስት እንዲህ አይነት ጠቃሚ ስልጠናዎችን በነፃ በመስጠት ወጣቱን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ የጀመረው ጥረት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን አንስቷል።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ዩኒት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ግርማ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮ ዓመት ከ4 ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል።
በስልጠናው ከተሳተፉት ውስጥ 3ሺህ 26 የሚሆኑት ስልጠናቸውን ሙሉ ለሙሉ አጠናቀው ሰርተፊኬት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026