የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ያነቃቁ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)- ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ያነቃቁ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቱሪዝም ዘርፉ 12 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልጿል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪስት ሃብት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች ከማስተዋወቅ ባለፈ አዳዲስ መዳረሻዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህም ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የክልሉን የቱሪሰት እንቅስቃሴ ያነቃቁ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከቱሪዝም ዘርፉ 12 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስረድተዋል።

በዚሁ ወቅት 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሃገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ሃብቶችን እንደጎበኙ ተናግረዋል።

የለውጡ መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል አንዱ ቱሪዝም መሆኑን ገልጸው ዘርፉን በተሻለ መጠቀም የሚያስችሉ በርካታ የልማት ሥራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ቱሪስቶቹ የፋሲል አብያተ መንግስታት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንን ጨምሮ ሌሎች መዳረሻ ቦታዎችን ጎብኝተዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ ገና፣ ጥምቀት፣ አገው ፈረሰኞች ማህበር በዓላት እንዲሁም በሃይማኖታዊና ባህላዊ ሁነቶች መታደማቸውንም ተናግረዋል።

የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠልም 27 ቅርሶችን የመጠገን፣ ቅርሶችን የማሰባሰብ፣ ሙዚየሞችን የመገንባትና መሰረተ ልማቶችን የማስፋት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በገበታ ለሃገርና በገበታ ለትውልድ የተገነቡት የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እና የሎጎ ሃይቅ ሪዞርት ተጨማሪ መዳረሻ ከመሆን ባሻገር ቱሪስቶች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙና የቆይታ ጊዜያቸው እንዲራዘም ያገዙ መሆኑን ገልፀዋል።

የተገኘውን ስኬት አጠናክሮ ለማስቀጠልም የዘርፉ የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት ዕቅድና የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ወጥቶ እየተተገበረ እንደሆነ አብራርተዋል።

በአሻጋሪ የልማት ዕቅዱ መሰረት ጣናን፣ ሰከላን፣ አንኮበርን፣ ጎንደርንና መሰል አካባቢዎችን መነሻ ያደረጉ 10 ወሳኝ አዳዲስ መዳረሻዎችን ለመገንባት መታቀዱንም አመልክተዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ #ቱሪዝም

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026