የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ለህብረተሰቡ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- መንግስት ለህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በየደረጃው ያለውን የዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ገለጹ።

የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።


በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፤ የተከናወነው የልማት ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱም በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ከምንም በላይ ለአፋር ህዝብ ውሃ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፤ የተደመረ አቅምን በማላቅና በማስተባበር ለውጤት የበቃው ይህ ፕሮጀክት በዚህ ረገድ ጉልህ አበርክቶ አለው ብለዋል።


በዛሬው ዕለት የተመረቁት ፕሮጀክቶች በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በዩኒሴፍ ድጋፍ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑንም አንስተው፤ ተቋማቱን አመስግነዋል።

በፕሮጀክቶቹ ተጠቃሚ የሆኑ ሁለቱ ወረዳዎች ለዘላቂነቱ ትኩረት በመስጠት በተገቢው ማስተዳደር እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ መንግስት እንደ አፋር ክልል ያሉ የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል ብለዋል።


ሚኒስትሩ አክለውም፣ በለውጡ መንግስት የተከናወኑ የተቀናጁ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በዚህም የአገራችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ወደ 72.5 በመቶ ከፍ ማለቱን አረጋግጠዋል።

የአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ አቶ አህመድ ሻሚ በበኩላቸው፤ የአይሳኢታ ከተማና የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያሳደገ ነው ብለዋል።


ፕሮጀክቱ የአይሳኢታና አፋምቦ ስምንት ቀበሌዎች ከ52 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎችና የአይሳኢታና አፋምቦ ወረዳ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት ከምስል ጋር!

  የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...

Jun 4, 2026

በዲጂታል ክህሎት ራሳችንን እያበቃን ነው - ተማሪዎች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...

Jun 1, 2026

በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል

አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...

May 25, 2026

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው

ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...

May 15, 2026