🔇Unmute
ባሕርዳር፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ተቋማቸው ባካሄደው የሪፎርም ትግበራ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የፍትሕ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው ገለጹ።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅትም አቶ ዓለምአንተ እንደገለጹት፤ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተቀረጸው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ አተገባበር ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የታቀዱ የመሠረተ-ልማት ዝርጋታ፣ የኔትወርክ ሥራዎች እና የስማርት ችሎቶች ግንባታ ሥራዎች በስኬት መከናወናቸውን አንስተዋል።
ይህም ባለጉዳዮች ባሉበት ሆነው በኢ-ፋይሊንግ ሥርዓት ክስ መመስረት፣ ይግባኝ መጠየቅና የጉዳያቸውን ሂደት በሞባይል መተግበሪያ መከታተል የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ሥራ ላይ መዋሉን አስረድተዋል።
በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚታገዙ ስማርት ችሎቶች በመዘርጋታቸውም ሕብረተሰቡ ካለበት ሆኖ ክርክሩን እንዲያካሂድ በማድረግ የባለጉዳዮችን ወጪና እንግልት መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር መኳንንት አገኘሁ (ዶ/ር)፤ የፍርድ ቤቶችን አሠራር ዘመናዊ በማድረግ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት፣ የፍትሕ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የዳኝነት አገልግሎት ጥራትን በማሻሻል የሕዝብን እርካታ ለማረጋገጥ ያስቻሉ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...
Jun 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...
Jun 1, 2026
አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...
May 25, 2026
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026