የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ አስገኝቷል

May 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ ማስገኘቱን ኢዜአ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች እና የነዳጅ ማደያዎች ገለጹ፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ተከስቶ የነበረውን ችግር ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ የተፈጠረው ክፍተት፣ በሀገር ውስጥም የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል አስከትሎ የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት አቅርቦቱ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ እንዲመለስ አድርጓል።

መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ የነበረውን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ተቋቁሞ ለማለፍ ያስቻለ ሲሆን፣ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች የተረጋጋ፣ ቀልጣፋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እንዲኖር አስችሏል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ የዓለም የነዳጅ ሁኔታን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፣ የናፍጣ ነዳጅ አቅርቦት ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ መደረጉን መጥቀሳቸው ይታወቃል፡፡

ኢዜአ በመዲናዋ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎችና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፤ መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደውን የማሻሻያ እርምጃ ተከትሎ በአቅርቦቱና በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ መታየቱን ገልጸዋል።


አስተያየት ከሰጡ አሽከርካሪዎች መካከል አባይነህ ይሁኔ፤ ቀደም ሲል ከዓለም አቀፉ የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ በነበረው መስተጓጎል በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ገጥሟቸው እንደነበር አስታውሰዋል።

አሁን ላይ ግን የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈትቶ ሁኔታው ወደ ቀድሞው በመመለሱ፣ በሁሉም ማደያዎች የሚፈልጉትን ያህል ነዳጅ ያለምንም እንግልት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


ሌላኛው አሽከርካሪ ከድር ሁሴን በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል ነዳጅ ለማግኘት እስከ አንድ ሳምንት ይወስድባቸው የነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ መፈታቱንና ያለምንም እንግልት ነዳጅ እያገኙ ማኅበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።


በተመሳሳይ አሽከርካሪ ተፈሪ ዓለሙ እና ረታ ጂቢቲ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው የነዳጅ እጥረትና የረጅም ሰዓት ወረፋ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በመቀረፉ፣ በአሁኑ ወቅት ያለምንም መስተጓጎል እየተስተናገዱ ይገኛሉ።


በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የነበረው ችግር በመወገዱ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠሩንና መደበኛ ሥራቸውን በተሻለና ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘሮች በበኩላቸው ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ምክንያት ይፈጠር የነበረው የአቅርቦት ችግር በመቀረፉ ደንበኞቻቸውን ያለምንም እንግልት እያስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በአቅርቦትና በስርጭት ላይ ችግር አለመኖሩን ጠቁመው ለማኅበረሰቡ ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በቡልጋሪያ አካባቢ የቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ሰለሞን ገብረሕይወት እና በአሮጌው ቄራ አካባቢ ቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ይርጋ ኪዳነ ማርያም ቀደም ሲል በነበረው እጥረት ምክንያት ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እስከ አምስት ቀናት የሚደርስ ረጅም ሰልፍ ይጠብቁ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ችግሩ ሙሉ በሙሉ መቀረፉን አረጋግጠዋል።


በተመሳሳይ የሜክሲኮ አካባቢ የካምፖ አስመራ ነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘር ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው፤ መንግሥት ዓለም አቀፉን የነዳጅ አቅርቦት ቀውስ ለማስተካከል የወሰደውን ቁርጠኛ እርምጃና የመጣውን ፈጣን አዎንታዊ ለውጥ አድንቀዋል።

በአሁኑ ወቅት ነዳጅ ለማደያቸው በአግባቡና በወቅቱ እየቀረበ መሆኑን ገልጸው እያገኙት ያለውን ምርትም ለተጠቃሚ አሽከርካሪዎች እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት ከምስል ጋር!

  የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...

Jun 4, 2026

በዲጂታል ክህሎት ራሳችንን እያበቃን ነው - ተማሪዎች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...

Jun 1, 2026

በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል

አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...

May 25, 2026

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው

ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...

May 15, 2026