🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የግብርና አቅሟን በአግባቡ ለመጠቀም እና የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የግብርና ምርምር፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሸጋገር እንደሚገባት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና ገለጹ።
በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 የማጠቃለያ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የፋኦ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ማዕከላት ጋር በየዕለቱ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።
በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማደራጀትና ለማስፋፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ዘርፉ የተለያዩ አቅሞችንና ሀብቶችን በተለየ መንገድ ማቀናጀትን እንደሚጠይቅ ገልጸው፣ በርካታ እድሎች ያሉት መሆኑንም አመላክተዋል።
ፋኦ ተልእኮውን መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል እንደ ድልድይና አቅም ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል።
የእውቀት ልውውጥ የሚደረግባቸው ቀጣይነት ያላቸው መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም የምርምር ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ተግባርና ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ አካሄድ ማስተዳደር ከተቻለ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል።
ገንዘብ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሰው ኃይል አቅምና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መንገድ ከሌለ በቂ እንደማይሆን አስረድተዋል።
በቂ ገንዘብ የተመደበላቸው አስፈላጊ ፕሮጀክቶች የታሰበውን ውጤት ሳያመጡ የቀሩት በገንዘብ እጥረት ሳይሆን በሰው ኃይል አቅም ማነስ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል።
በመሆኑም የፋይናንስና የሰው ኃይል አቅምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
አፍሪካ በርካታ እድሎች ያሏት አህጉር መሆኗን ጠቅሰው፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል።
በመሆኑም በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ በጋራ መሥራትና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ወደ ተቀናጀና ዘላቂ የሥራ አካሄድ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጥረቶች አንድ ጊዜ ብቻ ተከናወነው በሚያበቁ ፕሮጀክቶች ላይ ሳይወሰኑ፣ በቀጣይነት የሚሰፉና ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው።
በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዓለም ባንክ የግብርና ዋና ኢኮኖሚስት እና የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (CAADP) የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ቡድን ሊቀመንበር ሚዮ ታካዳ በበኩላቸው፣ የአለም ባንክ አግሪ ኮኔክት በተባለው ፕሮጀክቱ አማካይነት አርሶ አደሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል
ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰጡ የተናጠል ድጋፎችን በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እንዲኖር ማስቻሉን ተናግረዋል።

ለአርሶ አደሮች ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ከአቅርቦትና ከፍላጎት ጎን የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ፕሮግራም ኦፊሰር ዳንኤል ሂጊንስ ናቸው።
ይህም የግሉ ዘርፍ በቀጣይነት ድጋፉን እንዲረከብና በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋይናንስ ማድረጉን እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...
Oct 10, 2026
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026