🔇Unmute
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ እና ጨና ወረዳ የገጠር ሞዴል መንደር ነዋሪዎች ተናገሩ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ እና ጨና ወረዳዎች የተገነቡ የገጠር ሞዴል መንደሮችን ለነዋሪዎች አስረክበዋል።
የዚሁ እድል ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮችም በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል ሲሉ ተናግረዋል።

በሺሾ እንዴ ወረዳ የዳሔራ የገጠር ሞዴል መንደር ነዋሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ ገብረማርያም፤ የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ከምቹ መኖሪያነት ባለፈ ለእንስሳትና የግብርና ልማት ስራዎች የተመቻቹ በመሆኑ ምግባችንን በጓሯችን ለማምረት የሚያስችል ነው ብለዋል።
በመሆኑም በገጠር አዲስና ዘመናዊ ህይወት መኖር በመጀመራችን ተደስተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላኛው የመንደሩ ነዋሪ አቶ በቀለ በላቸው፤ ከዚህ ቀደም የእንስሳትና የሰዎች መኖሪያ የተለየ ስላልነበር ለጤና ችግር ይጋለጡ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ በሞደል መንደሮች ምቹና ዘመናዊ ኑሮ ጀምረናል ብለዋል።
በአዲስ ህይወት ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር ጠንክረው እንደሚሠሩ ገልጸው በተለይ የሌማት ትሩፋት ውጤቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።
በጨና ወረዳ የኮዳ የገጠር ሞዴል መንደር ነዋሪዎቹ አቶ ክፍሌ አንበሴ እና ወይዘሮ አየለች ተሰማ በበኩላቸው በአስር ዓመታት መሥራት የማንችለውን ቤት መንግስት በወራት ውስጥ ሠርቶ በማስረከቡ ተደስተናል እናመሰግናለንም ብለዋል።
የገቡበት አዲሱ ሞዴል መንደር ሁሉንም አይነት መሠረተ ልማት ያካተተ ሲሆን ይህም ማኅበራዊ ኑሯቸውን ቀላል የሚያደርግና ለልጆቻቸው የተሻለ ተስፋን ይዞ የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፤ የመደመር መንግስት የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል እያደረገ ባለው ጥረት የገጠር ሞዴል መንደሮች ለአርሶ አደሮች እየተበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በዞኑ እስካሁን ሦስት ሞዴል መንደሮች ተገንብተው ለነዋሪዎች መተላለፋቸውን ገልጸው በቀጣይ በሁሉም ወረዳዎች የማስፋፋት እቅድ ስለመኖሩም ገልጸዋል።
የገጠር ሞዴል መንደሮችን እንደማሳያ በመውሰድ ሌሎች አርሶ አደሮች በራስ አቅም የሚገነቡበት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026