የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

Aug 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

''የመንግሥትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የልማት አጋርነት ለላቀ እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ መንግሥትና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በማገዝ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይገባል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሪፎርም እሳቤና በመደመር መንገድ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያመጡ እንደሚገኙም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ መስኮች በመሳተፍ በመንግሥት ያልተሸፈኑ ክፍተቶችን በመሙላት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

በክልሉ ፈጣን እድገት ለማስመዝገብ የሁሉንም አካላት ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ ሲሆን ሀገሩን የሚወድ በስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋን ከመፍጠር ባለፈ የህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።


የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም በበኩላቸው፤ በክልሉ 97 የሚጠጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህጋዊ እውቅና አግኝተው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ድርጅቶቹ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

በተለይም በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በሰላም እሴት ግንባታ ዘርፎች ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ካፒታል ከ220 በላይ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ድርጅቶቹ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጀምሮ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር የጀመሩትን አጋርነት ሊያጠናክሩ እንደሚገባም ወ/ሮ ዘይቱና አሳስበዋል።

በዚሁ የምክክር መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴራልና የክልል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026