የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት በዘር ይሸፈናል 

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መርሐ ግብር ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት በዘር እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት ፍላጎቷ ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ይህንን የሀገር ውስጥ የፍጆታ ፍላጎት ለማሟላትም ለዓመታት ከ700 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሚደርስ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ለስንዴ ግዢ ስታወጣ ቆይታለች።

የኢትዮጵያ የለውጥ መሻት የወለደው የመደመር መንግሥት የዘመናት የተረጅነት እሳቤን ለመስበር የተገበራቸው የግብርና ልማት መርሐ ግብሮችም ከራስ ፍላጎት የተሻገረ የምርት አቅም ፈጥረዋል።


በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የተደረገው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል።

ይህም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገንዘብ ወጪ የምታስገባውን የስንዴ ምርት ሙሉ በሙሉ በማቆም ለውጭ ገበያ ማቅረብ የምትችልበትን አስተማማኝ ምኅዳር ገንብቷል።

በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ ገለቱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የግብርና ዘርፍ እመርታ የአርሶና አርብቶ አደሩን የዝናብ ጥገኝነት በማስቀረት አዲስ የልማት ባህል ፈጥሯል።

በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተበሰረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አርሶና አርብቶ አደሩ የተለዩ አማራጮችን በመጠቀም በዓመት ሦስት ጊዜ የሚያመርቱበትን ዕድል እንደፈጠረ ገልጸዋል።

ይህም ከዚህ ቀደም በደጋና ወይና ደጋ አካባቢ በአንድ ወቅት ብቻ ተወስኖ ነበረውን የስንዴ ሰብል ልማት ባህል በመስበር በሰፋፊ የቆላማ አካባቢዎች አዲስ የምርታማነት ባህል መፍጠሩን ተናግረዋል።


በዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መርሐ ግብር ሲበሰር የነበረው 20 ሺህ ሔክታር መሬት አሁን ላይ ከ3 ነጥብ 78 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በላይ ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ውጤታማ ልምምድም የአርሶና አርብቶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማላቅ የዘመናት የተረጅነት አስተሳሰብን የሰበረ አዲስ የምርታማነት ባህል መገንባቱን አብራርተዋል።

በ2018 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 3 ነጥብ 78 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በዘር በመሸፈን 149 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት እንደተቻለ አስታውሰዋል።

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መርሐ ግብርም ከሚቀጥለው ሕዳር ወር ጀምሮ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን 189 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026