የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

አዲስ አበባ የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት አሸነፈች

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦አዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የሰዎች ሰፈራ ፕሮግራም (UN-Habitat) በቻይና ያዘጋጀውን የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት ማሸነፏን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ይህ ድል ለአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው ብለዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የሰዎች ሰፈራ ፕሮግራም (UN-Habitat) በቻይና ያተዘጋጀው የሸንሃይ ሽልማት፣ በዘላቂ፣ አካታች፣ ሰው ተኮርና አይበገሬ የከተማ ልማት ውጤታማ ሥራዎችን ላከናወኑ በየዓመቱ ለአምስት ከተሞች የሚሰጥ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ነው ያሉት ከንቲባዋ በዚህም አዲስ አበባ በ2026 ከተሸላሚ ከተሞች አንዷ ሆናለች ብለዋል።

ይህ ለከተማችን የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2024 በUN-Habitat እና በደቡብ ኮሪያዋ ሴኡል ከተማ የተዘጋጀው “የሴኡል ከተማ ሽልማት”አሸናፊ መሆኗን አስታውሰዋል።


እነዚህ ተከታታይ ዕውቅናዎች በከተማ ልማት የተከናወኑ ሥራዎችንና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያመለክታሉ ብለዋል።

ሽልማቱ በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑት የከተማ ልማት ሥራዎች ውጤታማነት፣ ዘላቂነትና ለነዋሪዎች ያላቸው ጠቀሜታ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን እንደሚያሳይም ገልጸዋል።

ለዚህ ስኬት ካበቋት ዋና ዋና የልማት አቅጣጫዎች መካከል፦ሰው ተኮር አቀራረብን ከከተማ መልሶ ማልማት ጋር በማቀናጀት የነዋሪዎችን ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት፤ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሻሻል የተከናወኑ ሥራዎች፤ በከተማ ኮሪደሮችና በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች አካታችና የተቀናጀ ልማትን ማረጋገጥ፤ የትራንስፖርት አገልግሎትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎች፤ አረንጓዴነትን፣ ጽዳትንና የከተማ ውበትን በማሻሻል ምቹና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢ መፍጠር እንደሚገኙበትም አብራርተዋል።

እነዚህ ተግባራት የከተማዋን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማሳደግና አዲስ አበባን ተወዳዳሪ ከተማ በማድረግ ረገድ ያላቸውን አስተዋጽኦ ያሳያሉም ብለዋል።

በተለይም በታዳጊ አገራት ከባድ ፈተና የሆነውን የከተማ መልሶ ማልማት በስኬት ማከናወን እንደሚቻል ያሳየችው ተሞክሮ፣ ለሌሎች ከተሞችም ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ ምሳሌ ሆኗል ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ ድል የተግባር ስኬት፣ የጋራ ጥረትና የጋራ ውጤት ነውና ሁላችንም በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026