የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ማዕከሉ በአሲዳማነት የተጎዳ መሬትን በኖራ በማከም ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ማደግ እየሰራ ነው

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በአሲዳማነት የተጎዳ መሬትን በኖራ በማከም ለአርሶ አደሩ ምርታማነትና ተጠቃሚነት ማደግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊልና ጉመር ወረዳዎች ማኅበረሰብ አቀፍ የዘር ብዜት ማሳዎች ጉብኝት ተካሂዷል።


የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቤተል ነክር እንደገለጹት፣ ማዕከሉ በአሲዳማነት የተጎዳ መሬትን በኖራ በማከም ለአርሶ አደሩ ምርታማነትና ተጠቃሚነት ማደግ እየሰራ ነው።


ማዕከሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከማፍለቅ ባሻገር የዘር ብዜትን በማስፋፋትና በአሲዳማነት የተጎዳን መሬት በኖራ በማከም በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች እንዲሸፈኑ ማድረግ ማስቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ከምርት ውጪ የነበረን 72 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም በአጭር ጊዜ በሚደርሱ፣ በሽታንና አሲዳማ መሬትን በሚቋቋሙ ሰብሎች ማልማት መቻሉን አንስተዋል።

የጉመር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደገሙ አለሙ በበኩላቸው፣ ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

የግብርና ምርምር ተቋማት ቴክኖሎጂን በማፍለቅና በማስፋፋት፣ ዝርያዎችን በማባዛትና ተደራሽ በማድረግ በምርትና ምርታማነት ዕድገት ላይ ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።


የጉመር ወረዳ አርሶ አደር አቶ ዓለማየሁ አርጋው፣ ከዚህ ቀደም መሬታቸው በአሲዳማነት በመጠቃቱ ካላቸው 1 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት 25 ኩንታል ገብስ ብቻ ያገኙ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን በኖራ ከታከመው እስከ 40 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።


የምሁር አክሊል ወረዳ አርሶ አደር ነስሩ ከማል በበኩላቸው፤ ጦም ያድር በነበረ 15 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴን በኩታ ገጠም ለማምረት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም የምግብ ሉዓላዊነታቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ የስንዴ ምርጥ ዘር በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026