የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው

Nov 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን እርካታ በማሻሻል የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ አመርቂ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የፌዴራል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ገለጸ።

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ ማሞ አስታውቀዋል።

ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

የፌዴራል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ ማሞ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከ113 በላይ በሆኑ ማዕከላት ከ1 ሺህ 600 በላይ አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትም የተገልጋዮችን እርካታ 99 ከመቶ በማድረስ ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር መፈጠሩን ገልጸዋል።

በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ የመጣው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትም የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳለጥ የመልካም አስተዳደርን እያስፈነ መሆኑን አንስተዋል።

በቀጣይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመካር የጋራ መግባባት መደረሱን አብራርተዋል።

በመቀሌ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሲጀመርም ለክልሉ ሕዝብ ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ ዕድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሰመረ ጅራታ በበኩላቸው፤ አገልግሎቱ የማኅበረሰቡን እንግልት በማስቀረት ከፍተኛ ፋይዳ እያበረከተ ነው ብለዋል።


በክልሉም አራት የመሶብ አንድ ማዕከላትን ወደ ሥራ በማስገባት የተገልጋዮችን እርካታ ወደ 98 በመቶ ማድረስ ያስቻለ የተሳለጠና ዘመናዊ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመትም የመሶብ አንድ ማዕከላትን ወደ 14 ወረዳዎች ለማስፋት የዲዛይን፣ የቦታ መረጣ፣ የእድሳት ግምገማና የካፒታል ወጪ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብራርተዋል።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ አገልግሎት እየቀረበ ነው ያሉት ደግሞ የሲዳማ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንግዳየሁ ዘውዴ ናቸው።


በሐዋሳ ከተማና ሌሎች ከተሞች የተገነቡ የመሶብ አንድ ማዕከላትም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የአገልግሎት ልምምድን እያጎለበተ መሆኑን አንስተዋል።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ማዕከል ብዙ የመንግሥት አገልግሎቶችን በማቅረብ የዜጎችን የአገልግሎት ተደራሽነትና እርካታ በማሳደግ የሕዝብና መንግሥትን እምነት እያጎለበተ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026