🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ተከታታይ ሀገራዊ ዕድገትን ታሳቢ ያደረገና የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ረቂቅ በጀቱ ውጤታማ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ማሳካትና ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 29 መደበኛ ስብሰባ በአጠቃላይ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ዕቅድ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት የፌዴራል መንግስት በጀት በየዓመቱ እያደገ መምጣቱ የሀገሪቱን ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት አመላካች ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም በጀቱ ሀገሪቱ ያስቀመጠቻቸውን ግቦችና ስትራቴጂዎች ለማሳካት የምታደርገው የለውጥና የብልፅግና ጉዞን እውን ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።
የምክር ቤት አባላቱ ረቂቅ በጀቱ በዜጎች ህይወት ማሻሻል፣ በድህነት ቅነሳና የዜጎችን የመግዛት አቅም በማሻሻል ረገድ የተቀመጡ የአፈፃፀም መለኪያዎች ላይ የሚያመጣው ተጨባጭ ለውጥን በተመለከተ ማብራሪያ ጠይቀዋል።
የለውጡ መንግስት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ የሚያስችሉ ስራዎች መስራቱን ጠቅሰው የተጀመሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ የሚከናወኑ ተግባራት ምንድን ናቸው የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ለምክር ቤት አባላቱ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የ2019 በጀት ውጤታማ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ለማሳካት የሚያስችል ነው።
የኢኮኖሚ መረጋጋትና እድገትን የሚያሳልጥ ብሎም የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለልና ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን አንስተዋል።
የኢኮኖሚ አስተዳደሩን በማሻሻል አጠቃላይ የኢኮኖሚ መረጋጋትና የኢኮኖሚ እድገትን በማረጋገጥ በዜጎች ህይወት ላይ ውጤት እንደሚያመጣም ተናግረዋል።
በጀቱ ከሌሎች የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር በመቀናጀት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በማስቀጠል የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል።
ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስና የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጆችን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ማጽደቁም ይታወቃል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026