
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፡- አዲስ አበባ ከተማን ከሸገር ከተማ የሚያገናኙ አዳዲስ እና ነባር መንገዶች ግንባታ እና ማስፋፊያ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።
የመንገዶቹን ግንባታ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።
የሸገር ከተማን የሚያቋርጡ እና በሁሉም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶች ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ያለባቸው በመሆኑ መንገዶቹን ለማሻሻል የጥናት ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ችግሮችን በመፍታት የትራፊክ ፍሰቱን ለማስተካከል ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች ግንባታ በመካሄድ ላይ ነው ተብሏል።

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ አዲስ አበባ - ሆለታ መንገድ ማሻሻያ ፕሮጀከት፣ ከእንጦጦ ማርያም ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል እና ከስፔስ ኦብዘርቫቶሪ ጫካ መንደር ፕሮጀክት መንገዶች ግንባታን ጎብኝተዋል፡፡
የመንገዶቹ ግንባታ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል።
አዲስ አበባን ከሸገር ከተማ ከሚያገናኙ መንገዶች መካከል የጣፎ አደባባይ - ለገዳዲ - ኩራ - ጂዳ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ መሆኑንና ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመርም ተጠቁሟል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026