
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት 50 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና መከናወኑን የክልሉ መንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው በክልሉ የመንገድ ተደራሽነትን የሚያሰፉና ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚሳድጉ የመንገድ ልማትና ጥገና ስራ ሲያከናወን መቆየቱን ገልጿል።
በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በሚዘጋጀው 'ጉሚ በልበሎሚ' የውይይት መድረክ በመንገድ ጥገና እና የፕሮጀክቶች መጓተትና ጥራት ችግሮች እንዳሉ ተነስቷል።
የቢሮ ሃላፊ ጫላ አብዲ(ኢንጂነር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በሁሉም የክልሉ ዞኖች የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች እየተከናወነ ነው።
በክልሉ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም ከዋና ዋና መንገዶች ጋር የሚያገናኙ የመንገድ ግንባታና ጥገና መከናወኑን አንስተዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የመንገድ ፈንድ በማቋቋም 50 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ የመጠገኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም የመንገድ ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ የመንገድ ዝርጋታና ጥገና ላይ ሰፊ ስራዎችን እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በፌደራልና በክልሉ መንግስት መንገድ ፈንድ በኩል 7 ሺህ 44 ኪሎ ሜትር መንገድ ከባድና ቀላል ጥገና ለማከናወን በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን አስታውቀዋል።
ቢሮው የጥገና አቅሙን ለማጎልበት ባለፉት ዓመታት ግዙፍ የጥገና ማሽኖችን መግዛቱን አስታውሰዋል።
"ጉሚ በልበሎሚ" የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የህዝብ ጥያቄ በመሰብሰብና ሰፊ ጥናት በማካሄድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ምላሽ የሚጠይቅበት የውይይት መድረክ ነው።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026