
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፦ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ፍጻሜ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መቆም እንደሚገባ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ጽሕፈት ቤቱ ለኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች የግድቡ ግንባታ መሠረተ-ድንጋይ ለተቀመጠበት 14ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በመልዕክቱም፤ የግድቡ ግንባታ ለፍጻሜ መቃረቡን ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
ግድቡ በመላው ሕዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተከናወነ መሆኑ፣ ግንባታውም አንድነትን ማጠናከሩ፣ በደማቅ የዲፕሎማሲ ድል ታጅቦና የኢትዮጵያን ገፅታ በመገንባት ዘንድሮ 14ኛ ዓመቱን መያዙም ተጠቅሷል፡፡
ለዚህ ድል የበቃነው በኅብረት ችለን በመቆማችን ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ለሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች የበለጠ በጋራ መቆም እንዳለብን ለእኛም ትምህርት ለዓለምም ምሳሌ ነው ብሏል፡፡
የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍም ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጽሕፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026