
ነቀምቴ፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በ2017/18 መኸር እርሻ ከ800 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ገለጸ።
የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አስፋው ሀምቢሳ እንዳሉት፥ በመኸር አዝመራ ከሚታረሰው መሬት የተሻለ ምርት ለማግኘት የግብዓት አቅርቦት በስፋት እየተከናወነ ነው።
በዚህም በዞኑ ለመኸር እርሻ የሚውል ከ18 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር በሕብረት ስራ ማህበራት በኩል ለአርሶ አደሩ መቅረቡን ተናግረዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም እስካሁን ከ425 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር መዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን ጠቁመዋል።
ዘንድሮ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በሜካናይዝድ መንገድ የሚታረስ ሲሆን የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴም በስፋት እየተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በምርት ዘመኑ 808 ሺህ 200 ሄክታር መሬት በማልማት የተሻለ ምርት ለማግኘት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026