የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳዎች ከብሔራዊ እቅዶች ጋር ተጣጥመው እየተተገበሩ ነው

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሰኔ 11/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳዎችን ከብሔራዊ እቅዶች ጋር አጣምራ መተግበሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ ገለጹ።

ላላፉት ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተጠናቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ እንደተናገሩት፤ የተካሄደው መርሃ ግብር እንግዶችን በማስተናገድና ኹነቶችን በማካሄድ ስኬታማ ነበር።


የምዘና ስርዓትን ለማጠናከር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ የአገራት ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥና ትብብርን ለማጠናከር የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደተቻለም አብራርተዋል።

አገራት እንደየነባራዊ ሁኔታቸው የሚከተሉትን የምዘና ስርዓት በመድረኩ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስርዓትን ለመዘርጋት ያከናወነቻቸውን ተግባራት ማቅረቧን ገልጸዋል።

አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የልማት እቅዶችን ከብሔራዊ እቅዶቿ ጋር በማጣመርና የትግበራ ሂደታቸውን ሪፖርት፣ ክትትልና ግምገማ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።


ኢትዮጵያ እየተገበረች የምትገኘው የ10 ዓመት የልማት እቅድ እና አጀንዳ 2063 የዘላቂ ልማት ግቦችን አጣምሮ የያዘ መሆኑን በማስታወስ፤ በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በአገር ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔና ሪፎርም ማህበረሰብን ተጠቃሚ ማድረጉን ለማወቅ ጠንካራ የክትትልና ምዘና ስርዓት ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ተወካይ አምባሳደር ሞሃመድ ኢልአሚኒ በበኩላቸው፤ በአህጉሪቷ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም አፈጻጸሙን ክትትል በማድረግ ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


የአፍሪካ የግምገማ ማህበር በአጀንዳ 2063 ትግበራ በትብብር መስራቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው፤ አገራት ለአቅም ግንባታ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ግምገማ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚቼ ኦዲራጎ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሶስት ቀናት በአፍሪካ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔ መስጠት የሚያስችል የግምገማ ስርዓትንና ትብብርን የሚያጠናክሩ ኹነቶች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።


አንድነቷ የተጠናከረና በምጣኔ ሃብት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በዘላቂ ልማት ግቦችና አጀንዳ 2063 ለሚተገበሩ የልማት መርሃ ግብሮች ማህበሩ ከአገራት ጋር በትብብር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ከአፍሪካ እና ሌሎች የዓለም አገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጭዎችና ከ300 በላይ እንግዶች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026