
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት በየአካባቢው ያሉ ሀብቶችን በማልማት ያከናወናቸው ተግባራት ሀገራዊ ዕድገትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ያመላከተ ነው ሲሉ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ገለጹ።
በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ከተማዋን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጋት መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ አክለው ተናግረዋል።
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውንና በግንባታ ሥራ ላይ የሚገኘውን የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት ፕሮጀክት፣ የኮሪደር ልማት፣ የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የአዞ ራንች፣ አርባምንጮችንና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ነፃነት ጣሰው እንዳሉት፤ በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው የተከናወኑ የልማት ተግባራት ሀገር እምቅ ተፈጥሯዊ ሀብቷን በመጠቀም የልማት ጉዞ ላይ እንደምትገኝ ያመላክታል።
የልማት ሥራዎቹ እንደሀገር ለተጀመሩ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።

በተለይ በገበታ ለትውልድ እየተገነባ ያለው የአርባምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት ከተማዋን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ያደርጋታል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።
ፓርቲያቸው እንደሀገር በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር ከበደ አሰፋ በበኩላቸው፤ መንግስት በየአካባቢው መጪውን ትውልድ ታሳቢ አድርጎ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች አስደናቂ ናቸው ብለዋል።
እነዚህ ሥራዎች የተሻለች ሀገርን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚቻል የሚያረጋግጥ እንደሆነም ተናግረዋል።
የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ግራኝ ጉደታ በበኩላቸው፤ መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ እያከናወነ ያለው የልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው።

የሀገርንና የዜጎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሳሙኤል ብርሃኑ እንደተናገሩት፤ የተመለከቷቸው ስራዎች ሀገራዊ ልማትን የሚያመላክቱ ናቸው።
የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ተገኑ ደረጀ በበኩላቸው፤ የልማት ሥራዎች ሁለንተናዊ ልማት የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ከመንግሥት ጋር በትብብር እንሰራለን ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026