
አሶሳ፤ሐምሌ 12/2017 (ኢዜአ)፦ በ2018 በጀት ዓመት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት እንደሚከናወኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
ለሁለት ቀናት በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፤ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተሻለ አፈጻጸም በማስቀጠል በ2018 በጀት ዓመት ተጨባጭ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ይሰራል ብለዋል።
በክልሉ የገቢ አማራጭችን በማስፋት እና የአሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን የመንግሥትን የልማት ወጪ ፍላጎት ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የገቢ አሰባሰብ ላይ የታየው መሻሻል የልማት ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት አቶ አሻድሊ ባለሃብቶችን እና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን መታቀዱን ገልጸዋል።
በአሶሳ ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ወደ ሌሎች ከተሞች በማስፋት፣ የክልሉን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት እና በመጠቀም የክልሉን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የ2018 በጀት ዓመት እንደ ሀገር ትልልቅ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ የሚገቡበት መሆኑን ገልፀው ይህም ሀገራዊ ብልጽግና የሚረጋገጥበት መልካም አጋጣሚ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተጀመሩ ተግባራትን በሁሉም ወረዳዎች የማስፋት ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።
አመራሩ የተያዙ ዕቅዶችን ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት ለመስራት ራሱን ዝግጁ ማድረግ እንዳለበትም አቶ ኢሳቅ አሳስበዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026