
ባሕርዳር፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በ2018 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማስፈፀሚያ ከ225 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ ጥላሁን መሀሪ(ዶ/ር) ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በጀቱ የክልሉን የመልማት ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው።
በጀቱ የ2018 በጀት ዓመትና የ5 ዓመት የመካከለኛ ዘመን የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሰራዎችን ታሳቢ የተደረገ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የሪፎርም ስራዎችንና ሌሎች የትኩረት መስኮችን በጀቱ እንደሚያካተት ጠቅሰው፤ ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።
በጀቱ የሚሸፈነው በክልሉ የተለያየ የገቢ፣ ከፌዴራል መንግስትና ከሌሎች ምንጮች እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በጀቱ በትክክል የህዝብን የመልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቁጠባ ጥቅም ላይ እንዲውል ተገቢው ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ እንደሚደረግ ተመልክቷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፤ በጀቱ በፍትሃዊነት የተደለደለ በመሆኑ የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በቁጠባ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል።

በየደረጃው ያለው አመራር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የህዝብን የልማት ፍላጎት በአቅም ልክ ማከናወን ይገባል ብለዋል።
በዚህ በጀት ዓመት 25ቢሊዮን ብር ከህብረተሰብ ተሳትፎ በገንዘብ ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቅሰው፤ ይህ እንዲሳካ መረባረብ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የምክር ቤቱ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የቀረበውን ረቂቅ በጀትና የ2017 በጀት ዓመት 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መርምሮ አፅድቋል።
ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Jun 14, 2026
ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...
Jun 11, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...
Jun 4, 2026
ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...
May 25, 2026