
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፦ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እሴት በሚጨምሩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ መሰማራት የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አምና አልደሃክ(ዶ/ር) ጋር የሁለቱን ሀገሮች የግብርና ልማት ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትር ግርማ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ውይይቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችል ነው።
ኢትዮጵያ የቡና፣ የእንስሳት ውጤቶችና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ወደ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች እንደምትልክ ገልጸው፤ ግንኙነቱን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን አብራርተዋል።
ከዚህም ባለፈ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጎልበት የሁለቱ ሀገሮች ባለሀብቶች በመደበኛነት በሚገናኙባቸው መንገዶች ላይ መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የቴምር ምርትን ለማስፋት ከከሊፋ ፋውንዴሽን ጋር ውይይት መጀመሯን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ በመጭው ነሐሴ ወር ለመጀመሪያ ጊዜ የቴምር ጉባኤ እንደምታካሂድ ተናግረዋል።
የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባለሀብቶች በግብርናው ዘርፍ እሴት በሚጨምሩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሁለተኛው የተመድ የምግብ ስርዓት ጉባኤ ትኩረት የሰጠው ፋይናንስን ወደ ምግብ ሥርዓት እሴት ሰንሰለት ማምጣት ያለመ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አምና አልደሃክ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በሁለተኛው የተመድ የምግብ ሥርዓት ስብሰባ መሳተፋቸው ትልቅ ነገር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከስብሰባው ጎን ለጎን በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ሀገሮች በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ሊኖር በሚገባው ትብብር ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
ሁለቱ ሀገሮች በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ ስትራቴጂያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ውይይቱ ከሁለቱ ሀገሮች አልፎ ለቀጣናውና ለዓለም ብልጽግና ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026