የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢትዮጵያ ከዓለም ጋር ትገናኝበት የነበረውን የባሕር በር መጠየቋ ተገቢ ነው

Nov 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገራት ጋር ትገናኝበት የነበረውን የባሕር በር መጠየቋ መሠረታዊ ጥያቄ በመሆኑ ሁላችንም የሚጠበቅብንን መወጣት አለብን ሲሉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና ተመራማሪ አበበ አኖ (ዶ/ር) ገለጹ።

አበበ አኖ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ የሚደረገው ጥረት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የባሕር በር ከነበራቸው ቀደምት ሀገራት መካከል እንደነበረች አውስተዋል።

በነበራት የባሕር በርም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ጋር በንግድ፣ በጉብኝት እንዲሁም በሌሎች ሥራዎች ጥብቅ ቁርኝት እንደነበራት አስታውሰው፤ ይህንም ታሪክ እንደሚመሠክርም አስረድተዋል።

ነገር ግን ከዚህ ቀደም በነበረው የፖለቲካ ሁኔታ በተፈጸመ ታሪካዊ ስህተት የነበራትን ባሕር በር እንድታጣ መደረጉ አስቆጭም፤ አሳዛኝም መሆኑን ተናግረዋል።

በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ፍላጎት ሳይኖር በአንድ የፖለቲካ ቡድን ውሳኔ ብቻ የባሕር በርን ያህል ለዘርፈ-ብዙ ዕድገት ወሳኝ አበርክቶ ያለው ሐብት መነፈግ አንገብጋቢ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ቁጭት የሚፈጥረው ደግሞ ከለውጡ በፊት ለበርካታ ዓመታት የባሕር በር ጥያቄው በመንግሥት ደረጃ ‘ጆሮ ዳባ’ መባሉ ነው ይላሉ።

የሆነው ሆኖ የባሕር በሯ የተወሰደበትም ሆነ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም የተባለበት ሁኔታ ቢያስቆጭም፤ በለውጡ መንግስት ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት እንዳለባት ታምኖ አሁን ጥረቶች መጀመራቸው ተገቢ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የነበራትን ተቀምታ፣ ከቀይ ባሕር በቅርብ ርቀት ላይ ሆና፣ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ሆና እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይዛ የበይ ተመልካች ልትሆን እንደማይገባ አብራርተዋል።

ስለሆነም የራሷን ግዛት አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ያጣች ሀገር መሆኗን የሀገራት መሪዎች እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገንዝቦ እንዲያግዝ ሁላችንም የሚጠበቅብንን መወጣት ይገባናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብም የባሕር በር ለበለጸገች ሀገር አስፈላጊ መሆኑን ተረድቶ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መዋጣት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026