የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በድሬዳዋ የሠራተኛውን የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

የድሬዳዋ ፤ ህዳር 2/2018 (ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ የሠራተኛውን የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የአስተዳደሩ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ገለፀ ።

በድሬዳዋ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የመንግስት ሠራተኛውን የቴክኖሎጂ ክህሎት ለማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ቢሮው ከአስተዳደሩ የማዕከል ተቋማት የሰው ሃብት አመራሮች ጋር ዛሬ ተወያይቷል።


ውይይቱን የመሩት የቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የመሠረተ ልማት አቅርቦትና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ኢማድ አብዱልቀዩም፤ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሠራተኞችን የቴክኖሎጂ ክህሎት በማሳደግ የተገልጋዩን ፍላጎት ለማርካት እየተሰራ ነው።

የሠራተኛውን የቴክኖሎጂ ክህሎት ለማሳደግ ያልተቋረጠ ስልጠና እየሰጠ መሆኑንም አንስተዋል።

ስልጠናውም ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ የመገንባት ጉዞን ለማሳካት ቁልፍ ሚና በመጫወቱ ሠራተኞች በእድሉ እንዲጠቀሙ ከተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንተናግረዋል ።

የተሰጠውን ስልጠና በአግባቡ የወሰዱ ሰራተኞች በየተቋማቸው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመተግበር ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚህን አበረታች ስራዎች በላቀ መጠንና ፍጥነት ለማሳደግ የማዕከል ተቋማት የሰው ሃብት አመራሮች ተግተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

በቀጣይም ተመሳሳይ ውይይት በሁሉም ተቋማት በማካሄድ ሠራተኛው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናው ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ የሰው ሃብት አመራር ዳይሬክተር ወይዘሮ ማሾ መሐመድ በበኩላቸው፤ ሠራተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሠራተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በአግባቡ በመውሰድ ተገልጋይን ለማርካት በሚደረገው የአሰራር ሂደት ለውጥ ማምጣት እንደሚገባቸው የገለጹት ደግሞ የአስተዳደሩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የሰው ሃብት አመራር ዳይሬክተር ወይዘሮ ፌይሩዝ መሐመድ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026