የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በሶማሌ ክልል ከ340 ሺህ በላይ ዜጎች  የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ  አከናውነዋል

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅግጅጋ፤ ህዳር 3/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ከ340 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወናቸውን የክልሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።

በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምስራቅ ሪጅን የጅግጅጋ አካባቢ የምዝገባ አስተባባሪ አቶ ጌዲዮን ጌታቸው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን በተቀላጠፈ መልኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ኢትዮጵያ ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬታማነትም ቁልፍ ሚናን የሚጫወት ነው ብለዋል።


በዚህም በክልሉ የህብረተሰቡን የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታው ተሳትፎዋቸውን ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑን አቶ ጌዲዮን አስታውቀዋል።

በክልሉ ባሉት ዞኖችና በ66 ወረዳዎች በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፤ በባንኮች፤ በንግድ ማዕከላት እንዲሁም በሌሎች የመንግሥት ተቋማት ምዝገባው በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ፕሮግራሙ ከተጀመረ ከግንቦት 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን 340 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ከዚህ ውስጥ 180 ሺህ የሚሆኑት ከጅግጅጋ ከተማ ውጭ ባሉ ወረዳዎችና ዞኖች የተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።


በክልሉ እሰከ ሰኔ 2018 ዓ.ም ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመመዝገብ መታቀዱን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ወራት ብቻ ከ160 ሺህ በላይ ዜጎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የፕሮግራሙን ተደራሽነት በማስፋት ተጨማሪ የምዝገባ ማዕከላት ለመጨመር የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል የማሰማራትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ህብረተሠቡ ከምዝገባው በኋላ ከኢትዮ-ቴሌኮምና እውቅና ባላቸው ተቋማት ዲጂታል መታወቂያውን በመውሰድ በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026