🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ ሲንጋፖር በኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗ ከኢትዮጵያ ባለፈ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትስስር ማጎልበት የሚያስችላትን ማዕቀፍ እንደሚፈጥር የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ገለጹ።
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ላውረንስ ዎንግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር እና ለሲንጋፖር አዳዲስ የንግድ በሮች መክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም አመልክተዋል።
ትምህርት እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሀገራቱ ግንኙነታቸው ለማጠናከር ከሚፈልጉባቸው መስኮች መካከል እንደሚጠቀሱም አንስተዋል።
የሀገራቱ መሪዎቹ በተገኙበት ከቁልፍ የጋራ ፍላጎቶቻችን ጋር የሚጣጣሙ የክህሎቶች ልማት እና የካርቦን ገበያ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመናል ሲሉም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉትም ተናግረዋል።
የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል አመልክተዋል።
ሲንጋፖር እና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየተገነባ ነው ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026