የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የሆርቲካልቸር ምርቶች ለግብርናው ሁለንተናዊ  እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው

Nov 26, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦የአትክልት፣ፍራፍሬ እና አበባ ( ሆርቲካልቸር) ምርቶች ለግብርናው ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ሆርቲ ላይፍ ለርኒንግ በተሰኘ መርኃ ግብር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እ. ኤ. አ ከ2016 ጀምሮ በኢትዮጵያ እየሰራ ይገኛል፡፡

የድርጅቱን ውጤታማ ተሞክሮና ስኬቶች ወደ ሁሉም ክልሎች ለማስፋት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ የግብርና ሚኒስቴርና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡


በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር አሊ መሀመድ፤ የአትክልት፣ ፍራፍሬና አበባ ( ሆርቲካልቸር) ምርቶች ለግብርናው ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡

አትክልትና ፍራፍሬ ለምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ እንዲሁም ለአግሮ ኢንዱስትሪ ግብዓትነት እየዋሉ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡

ዘርፉ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለአረንጓዴ አሻራና ለኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል ፡፡

የኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እንዲሁም በአርሶ አደሩ ግብዓት አጠቃቀምና የግብርና ስራ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ፡፡

በስልጠናው በርካታ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውሰው ተሞክሮውን ወደ ሁሉም ክልሎች ማስፋፋት በሚቻልበት ጉዳይ ዙርያ ለመምከር መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪና የልማት ኮርፖሬሽን መሪ ፓውላ ሽናድለር፤ ድርጅቱ የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነት እንዲያድግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡


በመድረኩ የተገኙት አርሶ አደር መጣዓለም ፋንታሁን፤ በአትክልትና ፍራፍሬ አመራረት ዙሪያ በድርጅቱ አማካኝነት ስልጠና መውሰዳቸውን አስታውሰዋል፡።


በስልጠናው በመታገዝ አቮካዶ ፣ብርቱካን፣ ፓፓያና ማንጎ እያመረቱ እንደሚገኝ በመጥቀስ አሁን ላይ ለሎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ተናግረዋል።

በወሰዱት ስልጠና በትንሽ መሬት ብዙ ምርት ማምረት በመቻላቸው በአካባቢያቸው ለሚገኙ አርሶ አደሮች አርአያ ለመሆን መብቃታቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር ቀኑብሽ የሱፍ ናቸው ፡፡


የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት በሰባት ክልሎች በሚገኙ 200 ወረዳዎች 2 ሺህ 144 ተጠቃሚዎችን በመያዝ 31 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረጉ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026