የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በድሬዳዋ የቱሪዝም ሀብቶችን ጠብቆ በማልማት የዘርፉን ገቢ ይበልጥ  ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ የቱሪዝም ሀብቶችን ጠብቆና አልምቶ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የድረዳዋ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገለጸ።


የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ወንደሰን አባይ እንደገለጹት፤ በዘርፉ በተከናወኑት በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከ291ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ድሬዳዋን ጎብኝተዋል።

በአስተዳደሩ ስዕላዊ ጥበቦች ያሉባቸው የለገ ኦዳና ሌሎች ዋሻዎች እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ከ10ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የንግድ መተላለፊያ፣ የስልጣኔና የኃይማኖት ማዕከል በመሆን ያገለገለው ሐርላም የቱሪስቶች የስበት አምባ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል።

እስካአሁን 56 ቅርሶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተሰቷቸው መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህን ሃብቶች ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተገቢው መንገድ የመጠበቅ፣ የመንከባከብና የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

130 ዓመታት ላስቆጠረው የድሬዳዋ ምድር ባቡር ተርሚናል እና ለሐርላ የማሕበረሰብ ሙዚየም በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ድጋፍ ዕድሳት ተደርጎላቸው ለቱሪስቶች ምቹ መደረጋቸውን አስታውሰዋል።


በተጨማሪም ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የዱር እንሰሳትና አእዋፋት መገኛ የሆነውን የቀላድ ጥብቅ ደን ምቹ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን መሰራቱን ገልጸዋል።

በተቀናጀ መንገድ በትኩረት እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት የቱሪስት ፍሰትን በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።


በጽህፈት ቤቱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 'ሬጉላቶሪ' ቡድን መሪ አቶ ሰይፈ ስጦታው በበኩላቸው፤ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበረው የቁሉቢ ገብርኤል ንግስ በአል እና አመታዊ የድሬ ናፍቆት የዲያስፖራው ማሕበረሰብ በአልም ለቱሪስቶች መጨመር ጉልህ መደላደል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ከሐምሌ 2017ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 129ሺህ 300 የሀገር ውስጥ እና 16ሺህ 750 የውጭ ቱሪስቶች ድሬዳዋን መጎብኘታቸውን አንስተዋል።

ከዚህም ከ1 ቢሊዮን 869 ሚሊዮን ብር በላይ በተዘዋዋሪ ገቢ መገኘቱንና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችም እንዲነቃቁ ማገዙን ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማትን የመሳሰሉ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች መገንባታቸው በቀጣይም ከቱሪዝም ዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግ ያስችላሉ ነው ያሉት።

የአስተዳደሩ የቱሪዝም ሀብቶችን ጠብቆና ተንከባክቦ በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸወም ተገልጿል።

የቱሪዝም ሃብት ለአስተዳደሩ ሁለንተናዊ ዕድገት እና ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን ከምስራቅ ተጎራባች ክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026