🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2018(ኢዜአ)፦ የካዳስተር ቴክኖሎጂ ዘመናዊ የከተማ መሬት አስተዳደርና የውሳኔ አሰጣጥ አቅምን እያሳደገ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ገለጹ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንዳሉት፤ የካዳስተር መረጃ የከተሞችን የመሬት ሃብት በዘመናዊ አሰራር ሥርዓት ለመምራት ወሳኝ ነው፡፡
ባለፉት ሶስት ዓመታት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የመሬት ገጽታ በካዳስተር ሥርዓት ማደራጀት የሚያስችል ስኬታማ ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከተሞች ወሰኑ በምድርና በካርታ ላይ በግልጽ ተለይቶ የመጠቀም መብት የተረጋገጠለት ልዩ የመለያ ኮድ ያለው ስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊየን ቁራሽ መሬት ወይም ነጠላ የመሬት ይዞታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እስካሁንም በ150 ከተሞች ከሁለት ሚሊዮን በላይ ቁራሽ መሬት በካዳስተር ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
የካዳስተር ቴክኖሎጂ መልክዓ-ምድራዊ የመረጃ ከተሞች ተዓማኒ፣ ትክክለኛና የተናበበ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖራቸው እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የካዳስተር ቴክኖሎጂ የከተማ መሬትን ለሚፈለገው የልማት ዓላማ እንዲውል በማስቻል የዜጎችን ፍትሕዊ የይዞታ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
የካዳስተር ቴክኖሎጂ ምዝገባ ሥርዓት በዕቅድ የሚመሩ ዘመናዊና የገቢ አቅማቸው ያደገ ከተሞች እንዲፈጠሩ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጥናት ላይ የተመሰረተ የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታዎችን በማሳለጥ የከተሞችን ዕድገት እያፋጠነ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የአየር ላይ ቅየሳ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ከማሁ አብርሃም፤ የአየር ላይ ቅየሳ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኢትዮጵያ የመሬት ገጽታ በካዳስተር እንዲደራጅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በካዳስተር የቴክኖሎጂ ሥርዓት የተደራጁ የመሬት ገጽታ መረጃዎችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት እንዲቀረቡ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የመሬት ገጽታን በመለየት በአንድ ቋት መምራት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ቀሪ የመሬት ገጽታዎችን በካዳስተር ቴክኖሎጂ ሥርዓት አደራጅቶ ለመያዝ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026