🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡- ችግር ገፍቶ የሚጥለን ሳይሆን ገፍቶ የሚያስፈነጥረን መሆን አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።
በዚሁ ወቅትም፤ ችግሮች አሉ፤ ከዚያ ውስጥ መልካም ዕድሎችን ፈልቅቆ ማውጣት መቻል ይኖርብናል ብለዋል።
በችግር ትብታብ ታስረን እንዳንቀር ተስፈንጥረን ወደምንፈልገው ነገር እንድንደርስም በአንዳንድ ጉዳይ ላይ መደመራዊ ዝላይ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የመደመር ዝላይ ትኩረት ግን አራት ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚጠበቅበትም ነው ያስረዱት።
እነሱም ሰው ተኮር ትውልድ መር መሆን፣ ብዝኃ ዘርፍ ሀገር አቀፍ መሆን፣ በምክክር ተግባብቶ ፖለቲካዊ ዕልባት ማምጣት እንዲሁም ዕውቀት ሸማች ብልጽግና አምራች መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዱካ መከተል ቀላል ቢሆንም፤ ከሚፈለገው ግብ አንጻር በአጠረ ጊዜ ለመድረስ እንደማያስችልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።
መደመራዊ ዝላይ የሚያስፈልገው ክፍተትን (ጋፕን) ለመሙላት መሆኑን ጠቁመው፤ እመርታ ከመደመራዊ ዝላይ ውጭ ሊመጣ እንደማይችል አመላክተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026