🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦ በመደመር መንግሥት ዕይታ የገጠር ሽግግርን ለማረጋገጥ ውጤታማ የፖሊሲ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት "የገጠር ትራንስፎርሜሽንን በማሳደግ ውጤታማና ባለብዙ ዘርፍ የትብብር ተፅዕኖን ማጎልበት" በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት የገጠር ሽግግርን በማፋጠን የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል እየሰራ ነው።
በመደመር መንግሥት ዕይታ የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችም ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የገጠሩን የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ ማሻሻል አካታች ልማትና ዕድገትን የማረጋገጥ እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ የማሳደግ ጉዳይ በመሆኑ የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠን ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት።
የገጠር ሽግግርን ለማፋጠን ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ትብብራቸውን በመደመር እሳቤ የበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸውም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የኩታ ገጠም እርሻን በማስፋፋት የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው ብለዋል።

ገበያ-ተኮር የግብርና ምርቶችን በብዛትና በጥራት በማምረት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንባቸው አሰራሮች እየተተገበሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የ10 ዓመት የገጠር ትራንስፎርሜሽን ፖሊሲ ውጤታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል።
በመድረኩ የመንግሥት አመራሮች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የግብርና ዘርፍ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እንዲሁም የልማት አጋሮች የተገኙ ሲሆን፥ የገጠር ሽግግር ላይ ያተኮሩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ እንዲሁም በኢትዮጵያ የገጠር ሽግግርን ለማምጣት ያሉ ዕድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ባለድርሻ አካላት ምክክር ያደርጋሉ ተብሏል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026