🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተገማች፣ ግልፅና ምቹ የካፒታል ገበያ ምህዳር መፍጠሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እንደ ጀማሪ ሳይሆን እንደ ነባር ተቋም በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ነው።
የካፒታል ገበያ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለግሉ ዘርፍ የጎላ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።
በዚህም የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በተግባር የተገለጠ ውጤታማ ስራዎችን በብቃት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ገበያ መር የካፒታል ገበያ ዕድገት ለማምጣት የተመሰረተ መሆኑን በመግለፅ፤ በረጅም ጊዜ የግሉን ዘርፍ የፋይናንስ መሪ ለማድረግ የታለመ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተከናወነው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ተገማች ግልጽና ለገበያ ምቹ ምህዳር የፈጠረ መሆኑን በማንሳት፣ የባንኮችን የገንዘብ ክምችትን ማሳደግና ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
ከዚህም ባለፈ ተወዳዳሪና ገበያ መር የፋይናንስ ስርዓት ማንበር የሚያስችል ምህዳር ተፈጥሯል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ስርዓቱ መሳለጥ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ ብዝኃ የገበያ ስርዓትን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይኸውም ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ዕድገት አቀጣጣይ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች ያሉት ዋና ገዥው፤ ሪፎርሙ ምቹ የገበያ ምህዳር በመፍጠር ለኢትዮጵያ ብልጽግና የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተህልቁ በበኩላቸው፤ ባለስልጣኑ ህጋዊና ተቋማዊ ቅርፅ ይዞ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት የሚያዘምኑ በርካታ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉን ገልጸዋል።

ግቡን ለማሳካት ከቀጣናውና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠሩንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በካፒታል ገበያው ለሚሳተፉ በርካታ ተቋማት ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸው፤ ጠንካራ የካፒታል ገበያ ለመፍጠር ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ ጠንካራና ብቁ የካፒታል ገበያ ባለስልጣንን እውን ለማድረግ ሁሉም አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026