የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት የሠራተኞችን አቅም በማጎልበት ለብሔራዊ የምርታማነት ዕድገት ሚናውን ሊወጣ ይገባል

Dec 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የሠራተኞችን አቅም በማጎልበት ለብሔራዊ የምርታማነት ዕድገት ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።


በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ ግጭቶች፣ የኢኮኖሚ መናጋት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የቴክኖሎጂ መስተጓጎል በሥራ ከባቢ ላይ ጫና እያሳደሩ ነው።

በዚህ በተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታ የትምህርትና ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማስፋትና በአዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍሰት የዜጎችን ሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለተቋማት ግንባታ የተሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በተለይም የክህሎት ልማትን በማጠናከርና ምቹ የሥራ ምህዳር በመፍጠር በርካታ ወጣቶችና ሴቶችን በማብቃት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል።


የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገትና የሥራ ስምሪት የሠራተኞችን መብት የሚያስጠበቅ ምቹ ምኅዳር እንዲፈጠር ማስቻሉን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት በመንግስት የሪፎርም ሥራዎች ስኬት ወሳኝ አጋር ሆነው መቀጠላቸውንም አንስተዋል።

በቀጣይም ፈጠራን በማበረታታትና ብቁ የሰው ኃይል ግንባታን በማጠናከር የብሔራዊ የምርታማነት አቅም የማሳደግ ጉዞ ላይ አሻራቸውን ሊያሳርፉ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የመንግሥት፣ የሠራተኛ ኮንፌዴሬሽኖችና አሠሪ ማኅበራት ግንኙነትም በመተማመን፣ ግልጽነትና የጋራ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የሠራተኞችን ክብርና መብት በመጠበቅ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተሻለ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት አበክራ እየሠራች መሆኗንም አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026