የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያን ፍላጎቶች የሚያሳኩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና የሚያደርጓት የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

Dec 8, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ፍላጎቶች የሚያሳኩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና የሚያደርጓት የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ፡፡

''የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።


በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ሚሊዮን ማቲዎስ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ መንግስት የከተማዋን ብልፅግና እውን ለማድረግ የጀመረው ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ በነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ነዋሪዎች በተሰሩ የልማት ስራዎችና መሰራት በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።

ነዋሪዎቹ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተማዋን የቀየሩ እና የረጀም ጊዜ ችግሮችን የፈቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የከተማዋ የውሃ አቅርቦት ሁኔታ በውይይት መድረኩ ላይ ከተነሱት እና ምላሽ ካገኙ ጥያቄዎች መካከል ይገኝበታል።

የቤት አቀርቦት አሁን የከተማዋ ችግር ቢሆንም ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጡ ቤቶችን ገንብቶ ማስተላለፉ ተመላክቷል።

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ አሁንም ችግሮች መኖራቸውን ነዋሪዎቹ ያነሱ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ውይይቱን የመሩት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ(ዶ/ር) የብልፅግና ፓርቲ ዋነኛ አጀንዳ ለትውልድ የሚተላለፉ ልማቶችን ሰርቶ ማለፍ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የጉባ ብስራቶችን ባስቀመጥነው ጊዜ ፈጽመን የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማረጋገጥ እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።


የኢትዮጵያን ፍላጎቶች የሚያሳኩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና የሚያደርጓት የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ያብራሩት ደግሞ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ናቸው።

በብዙ መንገድ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በመነቃቃት ላይ ትገኛለች ለዚህም ለችግር የማይበገር ኢኮኖሚ እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ በነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ መንግስት የከተማዋን ብልፅግና እውን ለማድረግ የጀመረው የልማት ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026