🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018(ኢዜአ)፦የአምስት ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በመጨመር አማራጭ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለፀ።
የ5 ሚሊዮን ኢትዮ-የኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ይፋ የተደረገ የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርኃ ግብር ነው።
ኢኒሼቲቩ ለዜጎች በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰሎሞን ሶካ ለኢዜአ እንዳሉት መንግስት ቴክኖሎጂን የታጠቀ ማህበረሰብን በመገንባት ዓለም የደረሰበት የእድገት ደረጃን ለማስተካከል እየሰራ ይገኛል።
የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የዜጎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት እንዲጨምር በማድረግ ከሀገርም ባለፈ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆኑ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።
በዚህም ዜጎች ያገኙትን የቴክኖሎጂ እውቀት በመጠቀም በኦንላይን ስራ የመፍጠርና ተቀጥሮ የመስራት አማራጭ የስራ እድል እየፈጠረላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ስልጠናው ለዜጎች ሶስት መሰረታዊ የስራ አማራጮች መምጣቱ ገልፀው አንዱ የርቀት የስራ ስምሪት ወይም ፍሪላንሲንግ ሲሆን ሁለተኛው ተቋማት ቢዝነስ አውት ሶርስ በማድረግ የሚሰማሩበት ነው ብለዋል።
እንዲሁም ሶስተኛው ዜጎች ሀገር ውስጥ ሆነው ለውጭ ኩባንያ እንደ ወኪል የሚሰሩበት ሂደት መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኦን ላይን ስራው ብዙዎች ትልቅ ትኩረት ሰጥተውት እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው፤ የውጭ ምንዛሪ ከማምጣት ባሻገር ሀገር ውስጥ ያሉ ተቋማት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ባለፉት አራት ወራት 12 ሺህ 8 መቶ 75 ለሚሆኑ ዜጎች የርቀት ስራ መፍጠር መቻሉ ሚኒስትር ዴኤታው ጨምረው ገልፀዋል።
አሁን ላይ ዘርፉ በብዛትና በስፋት የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም የወጣቶች ትኩረት እየሳበና ወደ ስራ እያስገባ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
እንዲሁም በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ እንደ ራይድና ፈረስ ያሉ መተግበርያዎችን በመጠቀም በሚከናወኑ ስራዎች ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረ ነው ብለዋል።
በዚህም በራይድ ትራንስፖርት መተግበርያ ብቻ በመጠቀም ለ130 ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ላይ እየሰራችው ያለችው ስራ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ትልቅ ስንቅ እንደሚሆናት የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ማሳያ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ከአደጉ ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላት በመሆኑ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025