የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በኦሮሚያ ክልል 18 ሚሊዮን ኩንታል ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ ታህሳስ 1/2018(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል የቡና ምርትና ጥራትን በማስጠበቅ በምርት ዘመኑ 18 ሚሊዮን ኩንታል ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ እና የዞኑ አመራሮች በኢሉባቦር ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እየተሰበሰበ የሚገኘውን የቡና ምርት ጥራትና አያያዝ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የቡናን ምርታማነትና ጥራትን በማሻሻል በገበያ ተወዳዳሪነቱን የተሻለ ለማድረግ ኢንሼቲቭ ተቀርጾለት እየተሰራ መሆኑ ነው የተመላከተው።


የቡና ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግም ያረጁ የቡና ዛፎችን ከመጎንደልና በአዲስ ከመተካት ባለፈ፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞችን ማዘጋጀት ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።

ለዚህም በቡና ልማትና ጥራት ፓኬጅ ላይ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉም ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ እንዳሉት፤ በክልሉ የቡና ልማትና ጥራትን በማስጠበቅ በምርት ዘመኑ 18 ሚሊዮን ኩንታል ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው።

የቡና ጥራትን ለማረጋገጥ ቀይ እሸት ቡና በመልቀምና በአልጋ ላይ በማድረቅ በክምችትና በማጓጓዝ ብክለት እንዳይከሰት ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ በእስካሁኑ እንቅስቃሴ 8 ሚሊዮን ኩንታል መሰብሰቡን ተናግረዋል።


ከቡና የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግም ከቡና ልማት እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ ለምርት ጥራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በኢሉባቦር ዞን በቡና ከለማው 342 ሺህ ሔክታር መሬት በቡና መልማቱንና ከዚህም 74 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ‎አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ ናቸው።

በዞኑ በቡና ንግድ ስራ ላይ 22 ማሕበራት መሰማራታቸውንና ለጥራቱም ትኩረት እንዲሰጡ ግንዛቤ እንደተሰጣቸውም አስረድተዋል።


የቡና ምርት ጥራትን በማስጠበቅ የአምራቾች እና አቅራቢዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለማሳደግ ህገወጥ ንግድን መቆጣጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ እንዳልካቸው አንስተዋል።

በዞኑ የመቱ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ደሳለኝ ተፈሪና አቶ ገመቹ ተካ በበኩላቸው ቀይ ቡናን በመልቀምና በአልጋ ላይ በማድረቅ ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026