የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በአስተዳደሩ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት የሚያሳልጥ የቴክኖሎጂ አሰራር አቅም ተገንብቷል

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት የሚያሳልጥ የቴክኖሎጂ አሰራር አቅም መገንባቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

‎በአዲስ አበባ ከተማ 23 ወረዳዎች በኃይል መቆራረጥ የሚፈጠርን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት ምላሽ የሚሰጥ የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

‎በዚሁ ጊዜ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የመዲናዋን ነዋሪዎች የተቋማት የአገልግሎት ፍላጎት እርካታ የሚያረጋግጥ ዘመናዊ አሰራር እየተዘረጋ ነው ብለዋል።


በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፈጠረው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ የአሰራር ሥርዓት አቅም ለተገልጋዮች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሳለጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎በወረዳዎች የተገነባው የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክትም በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጠርን የአገልግሎት ክፍተት ምላሽ በመስጠት የደንበኛ እርካታን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በተለይም በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቋረጥ ለሚፈጠሩ የአገልግሎት ክፍተቶች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ አስረድተዋል።

በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሰራር የማስቀጠል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ፤ የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክቱ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶችን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

በቀጣይም አገልግሎት በሚበዛባቸው ወረዳዎች የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክቶችን በማስፋት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።


የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር)፤ የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክቱ በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጥርን የአገልግሎት ክፍተት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026