🔇Unmute
ባህርዳር፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ ዘመናዊ አኗኗርን መሰረት ያደረጉ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
ክልላዊ የተቀናጀ የገጠር ማዕከላት የቤት ልማት የንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅቱ እንደገለፁት በከተማም ሆነ በገጠር ዘመኑን የሚመጥኑ፣ ለኑሮ የሚመቹ ቤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።

የቤት አቅርቦት ችግርን በመፍታት ዘመናዊ ቤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ከፌዴራል የቤት አቅርቦት ፖሊሲ ጋር የተናበበና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ የቤት መሰረተ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
የገጠር ቤት ልማትና ደረጃን በማሳደግ ወደ ከተማ የሚፈልሰውን የሰው ሃይል ለመቀነስና ሀብት የሚፈጥርበትን እንዲሁም ዘመናዊ አኗኗርን የሚላመድበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም አመራሩ የህብረተሰቡን የመኖርያ ቤት እጥረት ለመፍትት በገጠርም ሆነ በከተማ ዘመናዊ አኗኗርን መሰረት ያደረጉ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ የገጠር ኮሪደር ልማትን ተደራሽ ማድረግ፣ ሁሉን አካታች የገጠር ማዕከላትን ማስፋት፣ በከተሞች የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለተግባራዊነቱም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ(ዶ/ር) በበኩላቸው የገጠር ማዕከላትንና አካታች መንደሮችን በማስፋት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማቃለል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የከተማ ቤት አቅርቦት ችግርን ከመቅረፍ ባለፈ የገጠር ቤቶችን ዘመኑን የዋጁ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም የክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026