🔇Unmute
መቱ ፤ ጥር 14 /2018(ኢዜአ)፦በኢሉአባቦር ዞን በኢኒሼቲቭ መልክ እየተተገበረ የሚገኘውን የፍራፍሬ ልማት ለማስፋት የችግኝ ዝግጅት በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
የኢሉአባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቻላቸው አዱኛ፣ በዞኑ በኢኒሼቲቭ መልክ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓያ በስፋት እየለማ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ ከ32 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ላይ የፍራፍሬ ልማት እየተከናወነ ሲሆን ከሚለማው መሬት ውስጥ 28 ሺህ ሔክታር ላይ የሚገኘው ምርት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

ስራውን የበለጠ ለማፋፋትም በ220 የመንግስት የችግኝ ጣቢያዎችና በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የችግኝ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑ ከግብርና ምርምር የወጡ የአቮካዶ፣ የሙዝና የሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች የተዘጋጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
በችግኝ ማፍላት ስራው ከ42 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል።
በበጋው ወራት የተዘጋጁት እነዚህን ችግኞች በተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ በተሰራበት መሬት ላይ እንደሚተከሉም ገልጸዋል።

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡት እነዚህ ችግኞች የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እንደሚያግዙም አስረድተዋል።
ጥምር ጥቅም በሚሰጡ ችግኝ ማፍላት ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል በዞኑ በሁሩሙ ወረዳ የሎኮ ሳያ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ተካልኝ ታደገ እንዳሉት፤ አቮካዶና ሙዝ በማምረት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ ነው።

ስራውንም የዛሬ ሁለት ዓመት በበጋ ወራት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በተከናወነባቸው ሩብ ሔክታር መሬታቸው ላይ በመተግባር መጀመራቸውን አስታውሰዋል።
የፍራፍሬ ግብርናው በትንሽ ማሳ ላይ የምግብ ዋስትናና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ አቅም እንደሆናቸው አንስተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026