የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በልማትና መልካም አስተዳደር ዘርፎች ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል

Jan 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ ጥር 14/2018(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በልማትና መልካም አስተዳደር ዘርፎች ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።


የክልሉ መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት አፈጻጸም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተገመገመ ነው።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ቃሲም ኢብራሂም የክልሉን መንግስት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል።

በሪፖርታቸውም ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን 5 ቢሊዮን 194 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንና 4 ሺህ 158 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን በተሻለ አፈጻጸም አንስተዋል።


ይህም በክልሉ እየተከናወኑ ላሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እና ለሌሎችም የልማት ተግባራት ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር እንደሚያስችል አንስተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አሻድሊ ሀሰን፤ ባለፉት ስድስት ወራት ከክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ጋር የተመጣጠነ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የኢንቨስትመንት አቅሞችን በማልማት የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት በሰፊው እየተተገበሩ መሆኑን አንስተው፤ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


በቴክኖሎጂ የታገዘ የአገልግሎት አሰጣጥን በማስፋት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የሚያስችሉ ተግባራትም ተከናውነዋል ብለዋል።

በከተማ እና በገጠር እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በላቀ የህዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፥ በሌማት ትሩፋት እና ሌሎች የልማት ኢንሼቲቮችም ቀጣይነት ያለው ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን አንስተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑትን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ፍጥነትና ፈጠራ በታከለበት መንገድ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026