🔇Unmute
ከሚሴ፤ የካቲት 1/2018(ኢዜአ):- በአማራ ክልል የፋይናንስ ስርአቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠንና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ገንዘብ ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በከሚሴ ከተማ እያካሄደ ነው።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን እንደገለፁት፣ የክልሉን ገቢና ወጭ በማጣጣም ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

ለዚህም የፋይናንስ አጠቃቀምን ዲጂታላይዝ በማድረግ በሀብት አጠቃቀምና በሌሎችም አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
በተለይም በመንግስት ግዥ፣ በውስጥ ኦዲት፣ በወጪ አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጡ ግልጸኝነት ያለው አሰራርን በመዘርጋት ለክልሉ ዘላቂ ልማት እንዲውል አግዟል ብለዋል።
በክልሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው፣ ለውጡ የፋይናንስ ተቋማትን ማዘመኑ ሀብትን በአግባቡ በማስተዳደር ልማት ላይ እንዲውል አስችሏል ብለዋል።

በዚህም በዞኑ የተለያዩ የበጀት ምንጮችን በአግባቡ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።
የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሀብት፣ ንብረትና ግዥ አሰራሩን ማሻሻል ተችሏል ያሉት ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ነጋ ናቸው።
ገንዘብ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የተጠናከረ ቁጥጥር እየተደረገ ነውም ብለዋል።
የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላይነህ ወንድም አፈራሁ በበኩላቸው፣ የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ መቻሉ ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት አስችሏል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ለህብረተሰቡ ተአማኒነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚካሄደው መድረክ ላይም የክልሉና የዞን አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026