🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ):- የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአህጉሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ማጠናከርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት በአዲስ መልክ ለማደስ እንደሚሰሩ አስታወቁ።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ባንኩ ለአፍሪካ ቁልፍ የትኩረት መስኮች እያደረገ ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 11 ቢሊን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን መልካም የሚባል እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል።
ሊቀመንበሩ እና የባንኩ ፕሬዝዳንት ከእዳ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የደህንነት ፈተናዎች ባለፈ የፋይናንስ አቅርቦት የአፍሪካ አበይት ፈተና መሆኑን በምክክራቸው ወቅት ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች የፕሮጀክት ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር፣ የአንድ ትሪሊን የአሜሪካን ዶላር የአፍሪካ ካፒታል ማሰባሰብ፣ የአፍሪካ የብድር ምዘና ኤጀንሲን ማጎልበትና ጠንካራ የአፍሪካ የፋይናንስ ስርዓት መገንባት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ ተሠማመተዋለ።
በዓመት ሁለት ጊዜ ለመወያያት እና በአፍሪካ ፋይናንስ ላይ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ለማካሄድ እቅድ መያዛቸውንም ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026