🔇Unmute
ዲላ ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተሳፋሪዎች የሚነሱ ልዩ ልዩ ቅሬታዎችን በዘላቂነት እንደሚቀርፍ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ አስራ ስድስት ከተሞች ተግባራዊ የሚደረገው የኢ-ትኬት የትራንስፖርት አገልገሎት ዛሬ በዲላ መናኸርያ በይፋ ተጀምሯል።
የቢሮው ኃላፊ ተወልደ ተስፋዬ ፤ በክልሉ የተጀመረው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተሳፋሪዎች የሚነሱ ልዩ ልዩ ቅሬታዎችን በዘላቂነት እንደሚቀርፍና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል።

በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተለይ ዲላን ጨምሮ በክልሉ ሶስት ከተሞች ዘመናዊ መናኸሪያዎች ግንባታ ለማከናወን ዝግጅት ከማድረግ ባለፈ አራት የደረቅ ጭነት መናኸሪያዎች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በከተማው ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች በዲጂታል በማስደገፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር) ናቸው።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026