የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ፕሮግራሙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ለአካባቢ ውበትና ገጽታ ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ነው

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ የካቲት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እየተተገበረ ያለው የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ለአካባቢ ውበትና ገጽታ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ።

የኦሮሚያ ክልል የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም በክልሉ በ30 ከተሞች እየተተገበረ ይገኛል።

ፕሮግራሙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለአካባቢ ጥበቃና ለገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ተሳታፊዎቹ በአረንጓዴ ልማት፣ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ላይ በመሰማራት ለከተሞች ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አመልክተዋል።

ፕሮግራሙ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና በቤተሰብ ደረጃ ጥሪት ለማፍራት እያስቻለ መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።

ተሳታፊዎቹ በቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ዘዴዎች ላይ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉንና ከሚያገኙት ገቢ ላይ እንዲቆጥቡ ብድር እንዲያገኙና የመሥሪያ ቦታ እንዲመቻችላቸው እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም በክልሉ በሁለት ዙር የተመለመሉ 150 ሺህ ዜጎች የሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ አግኝተው በከተማ ግብርና፣ በንግድና በማምረቻው ዘርፎች ተሰማርተው ኑሯቸውን ማሻሻል መቻላቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን የሥራና የቁጠባ ባህል ማሳደጉን፣ አረጋውያንንና አቅመ ደካሞችን በቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ ማድረጉን፣ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና መንግሥት የጀመረውን ከተረጂነት ወደ አምራችነት የመሸጋገር አቅጣጫ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የአማራ ክልል የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አስተባባሪ ሀሰን ኑሩዬ በበኩላቸው፤ በክልሉ በ18 ከተሞች እየተተገበረ በሚገኘው በዚህ ፕሮጀክት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት ለመቀየርና የሥራ ባህልን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ዜጎች በፍትሃዊነት ተለይተው በከተማ ግብርና፣ በሌማት ትሩፋትና በሌሎች አዋጭ የሥራ መስኮች እንዲሰማሩ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ 239 ሺህ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ዜጎች ሠርተው ከድህነት እንዲወጡ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ሲሉም ገልጸዋል።

በሁለት ዙር ከ24 ሺህ በላይ ዜጎች በፕሮግራሙ ተመርቀው መውጣታቸውንና በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮችም መሠረታዊ የኑሮ ለውጥ ማሳየታቸውን አብራርተዋል።

የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ድህነትና ሥራ አጥነትን በመቀነስ፣ የከተሞችን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ እንዲሁም የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ በኩል ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026