🔇Unmute
ሆሳዕና ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በከምባታ ዞን ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ ፕሮጀክቶች የነበሩባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳድጉ መሆኑን የዞኑ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበልግ ወቅት ከ208 ሺህ 602 ሄክታር በላይ መሬት ይለማል
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የመስኖ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድና የተንጠልጣይ ድልድይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ አጠናቆ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች በዚህ ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ ፕሮጀክቶች የነበሩባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡
በዞኑ የሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር በለጠ ሾቢሶ፤ በአካባቢያቸው ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የሳቶራ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቀው በመስኖ ልማት እንዲሳተፉ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከመደበኛ የግብርና ስራቸው በተጨማሪ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በወቅት ሳይገደቡ አልምተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግም ገልጸዋል፡፡
በቃጫቢራ ወረዳ መሳፌ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር አስፋው አንሼቦ በበኩላቸው፤ በአካባቢያቸው የመንገድ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ የሚያመርቱትን ምርት ለገበያ ለማቅረብም ሆነ ማህበራዊ አገልግሎት ለማግኘት ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ያጠናቀቀው መንገድ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ የግብርና ምርታቸውን በቀላሉ ወደ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው የንፁህ ውጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በመኖሩ ከወራጅ ወንዝ በመጠቀም ለተላላፊ በሽታዎች ይጋለጡ እንደነበር የገለጹት ደግሞ በዞኑ የዶዮገና ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ብዙነሽ ኃይለ ማርያም ናቸው፡፡

በአካባቢው ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም የነበረባቸውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት ሙሉ በሙሉ የሚቀርፍ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ እንደገለፁት፤ በክልሉ መንግስት የተገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመስኖ፣ የመንገድና የተንጠልጣይ ድልድይ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረግ የዞኑ ማህበረሰብ በሁሉም ዘርፍ ያለውን አቅም እንዲጠቀምና ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችለው ስለመሆኑም አመልክተዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በቅርቡ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026