🔇Unmute
ሀዋሳ ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
በክልሉ በስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ላደረጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ተካሄዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ለተገኙ ውጤቶች የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ ነው።
የክልሉ መንግስት የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም ስራ አጥ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት በሚደረገው ጥረት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የፋይናንስና የክህሎት ስልጠና በመስጠት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ መንግስት ከአጋር አካላት ጋር የጀመረውን ቅንጅት በማጠናከር በዘርፉ የሚከናወነውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው፤ በክልሉ በስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ዘርፍ ለተገኙ ውጤቶች የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራን በመተግበር ሂደት የክህሎት ልማት ላይ የተከናወኑ ተግባራት በዘርፉ ለተገኘው ውጤት ጉልህ ሚናን አበርክቷል ብለዋል።
የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ኢንዱስትሪውን እንዲቀላቀሉ በሚደረገው ጥረት የማምረቻና መሸጫ ቦታዎችን በማዘጋጀትና የማሽነሪ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል።

የዛሬው መድረክ ዋና ዓላማም እስካሁን ለተከናወነው ተግባር ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት ቅንጅቱን የማጠናከር ስራ ለመስራት ነው ብለዋል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አጋር አካላት በተያዘው በጀት ዓመት ከ39 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስልጠና ድጋፍ ማድረጋቸውም ታውቋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026